የመጀመሪያ ቀን
icon
የመጨረሻ ቀን
icon
አካባቢ
አዲስ አበባ
በቀን 25/11/2016
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከዋናው ቢሮ እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች በዚህ ክረምት ለ3ኛ ዙር የችግኝ ተከላ ያካሄዳል።
በ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ!" በሚል መሪ ሀሳብ በሀገራችን አና በከተማች እየተካሄደ ባለበት ወቅት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከዋናው ቢሮ እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ 20 ሺ የሚጠጉ ችግኞችን ለ3ኛ ዙር ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በአቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ተከላ አካሂደዋል።
በዕለቱም የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን በሚያስጀምሩበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ በአሁኑ ወቅት ከተማችን አዲስ አበባን እንደ "ስሟ ውብና አበባ" ለማድረግ እየተከናወነ ከሚገኘው የኮሪደር ልማት ጎን ለጎን አረንጓዴ ለማልበስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በንቃት በመሳተፍ ከተማዋን ለማልማት በሚደረገው ተሳትፎ የበኩሉን ለመወጣት ጠንክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል፡፡